Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ ዘላቂ ሰላም በማስፈን የሕዝቡን የእርስ በርስ ግንኙነት ለማጠናከር እየተሰራ ነው – አቶ ኡሞድ ኡጁሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ከኢታንግ ልዩ ወረዳ አመራሮችና የህብረተሰብ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷በክልሉ ተፈጥሮ የነበረው የፀጥታ ችግር በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ በመወገዱ ህብረተሰቡ የዕለት ተዕለት ተግባሩን ያለምንም ስጋት እያከናወነ ይገኛል።

በክልሉ ዘላቂ ሰላም በማምጣት የህዝቡን የእርስ በርስ ግንኙነት ለማጠናከር መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

በልዩ ወረዳው አንዳንድ አካባቢዎች የመማር ማስተማር ስራ እንዳልተጀመረ ጠቁመው÷ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ እንዲገባ አሳስዋል።

የትምህርት ሥራው ያለምንም ችግር እንዲካሄድም ባለድርሻ አካላት ተገቢውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኢታንግ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች በበኩላቸው÷ ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት በመሆኑ ለክልሉ ዘላቂ ሰላም መስፈን በጋራ እንሰራለን ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.