Fana: At a Speed of Life!

ተመድ በእስራኤል እና ፍልስጤም ጉዳይ ላይ አስቸኳይ ልዩ ስብሰባውን ሊቀጥል ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የእስራኤል እና ፍልስጤም ግጭትን አስመልክቶ 10ኛ የአስቸኳይ ጊዜ ልዩ ስብሰባ እንደሚቀጥል የጉባኤው ፕሬዚዳንት ዴኒስ ፍራንሲስ አስታወቁ።
የአረብ ቡድን ሊቀመንበር እና የእስላማዊ ትብብር ድርጅት ሊቀመንበር የሆኑት በተመድ የዮርዳኖስ አምባሳደር ማሃሙድ ሁሙድ እና በተመድ የሞሪታንያ አምባሳደር ሲዲ መሀመድ ላግዳፍ በፈረንጆቹ ጥቅምት 19 ቀን በፃፉት ደብዳቤ በተቻለ ፍጥነት 10ኛው አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ እንዲጀመር መጠየቃቸውን ፕሬዚዳንቱ ለልዑካን ቡድኑ በፃፉት ደብዳቤ ገልፀዋል፡፡
ከኒካራጓ፣ ሩሲያ እና ሶሪያ ተወካዮች እንዲሁም ከባንግላዴሽ፣ ካምቦዲያ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ላኦስ፣ ማሌዥያ፣ ማልዲቭስ፣ ቲሞር-ሌስቴ፣ ቬትናም እና ብሩኒ ተወካዮችም ተመሳሳይ መልዕክት የያዘ ደብዳቤ እንደደረሳቸውም ጠቅሰዋል።
በዚህም 39ኛውን ምልአተ ጉባኤ 10ኛ የጠቅላላ ጉባኤ አስቸኳይ ጊዜ ልዩ ስብሰባ በፈረንጆቹ ጥቅምት 26 ቀን መጥራታቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል።
ተመድ 10ኛ አስቸኳይ ልዩ ስብሰባውን በፈረንጆቹ 1997 ለመጀመሪያ ጊዜ ያደረገ ሲሆን፥ በፈረንጆቹ 2018 ደግሞ ለመጨረሻ ጊዜ ማድረጉ ይታወሳል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.