Fana: At a Speed of Life!

በጀርመን ሰሜናዊ ባህር ዳርቻ መርከቦች ተጋጭተው በርካቶች መጥፋታቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀርመን ሰሜን ባህር ዳርቻ ሁለት ዕቃ ጫኝ መርከቦች ተጋጭተው በርካታ ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም ሲሉ የጀርመን ባለስልጣናት ገለፁ።
ዛሬ ማለዳ ላይ የብሪታንያ ሰንደቅ አላማ የሚያውለ በልብ ቬሪቲ የተሰኘ መርከብ ፖለሲ ከተሰኘ የባሃሚያን መርከብ ጋር በመጋጨቱ ሳይሰጥም አልቀረም ተብሏል።
ቬሪቲ ከሰሜናዊው የጀርመን ከተማ ብሬመን ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ኢሚንግሃም በመጓዝ ላይ ሳለ ከሀምቡርግ ተነስቶ ወደ ስፔን ላኮሩኛ በመጓዝ ላይ ከነበረ የፖለሲ ቡድን ጋር መጋጨቱ ተገልጿል።
አደጋው የተከሰተው የሻለስዊግ-ሀለስታይን ግዛት አካል በሆነው በጀርመን ደሴቶች ሄሊጎላንድ የባህር ዳርቻ ላይ መሆኑ ተመላክቷል።
የጀርመን የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ከሰባት የቬሪቲ መርከበኞች አንዱን መታደግ መቻሉን የገለጹ ሲሆን፥ የባህር ላይ የድንገተኛ አደጋዎች ማዕከላዊ አዛዥ ደግሞ ሌሎች ስድስት ሰዎች እንደጠፉ መግለጹ ተጠቅሷል፡፡
የጀርመን የባህር ኃይል የአሰሳ እና ነብስ አድን አገልግሎት፣ የጀርመን ባህር ኃይል ሄሊኮፕተር እና የውሃ ላይ የፖሊስ ጀልባዎች በፍለጋው ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸው ተነግሯል።
በአቅራቢያው የሚገኝ የሽርሽር መርከብም አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።
እስካሁን የአደጋው መንስኤ ምን እንደሆነ የታወቀ ነገር አለመኖሩም ተመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.