Fana: At a Speed of Life!

አይኤምኤፍ የእስራኤል-ሃማስ ጦርነት የቀጣናውን ምጣኔ ሀብት እየጎዳ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእስራኤል እና በሃማስ መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት በቃጣናው ያሉ ሀገራትን ምጣኔ ሀብት እያናጋ ነው ሲሉ የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ ተናገሩ።
የባለሀብቶች ጉባኤ በሳዑዲ አረቢያ ዋና ከተማ ሪያድ እየተካሄደ ነው፡፡
በጉባኤው የተገኙት ዳይሬክተሯ ጦርነቱ እንደ ግብፅ፣ ሊባኖስ እና ዮርዳኖስ ባሉ ጎረቤት ሀገራት የምጣኔ ሐብት እንቅስቃሴ ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡
የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን ሃማስ በፈረንጆቹ ጥቅምት 7 በእስራኤል ላይ ጥቃት በማድረስ ከ1 ሺህ 400 በላይ ሰዎችን ለህልፈት በመዳረግ 222 ሰዎችን አግቶ እንደወሰደ የእስራኤል ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
ይህንንም ተከትሎ እስራኤል የአየር ድብደባ እና አጠቃላይ የጋዛን ምድር፣ ባህር እና አየር በመዝጋት ምላሽ መስጠቷንም አመላክተዋል፡፡
በሀማስ የሚመራው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በጦርነቱ እስካሁን 5 ሺህ 791 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ማስታወቁንም ጠቁመዋል።
ዳይሬክተሯ አያይዘውም ጦርነቱ በተለይም ወደሌሎች ሀገራት የሚዛመት ከሆነ በዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ላይ ከባድ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል ማስጠንቀቃቸውን ሊጂት የዜና አውታር ዘግቧል።
የሚታየው ነገር ቀድሞውንም በውጥረት ውስጥ ላለችው ዓለም የባሰ ችግር የሚጨምር ነው ሲሉም ጆርጂዬቫ ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.