ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ116ኛው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ቀን ያስተላለፉት መልዕክት ዋና ዋና ነጥቦች On Oct 26, 2023 1,042 -እንደስሙ የመከላከያ ሠራዊት የሆነው ኃይላችን በመቶ አመት ታሪኩ ማጥቃትን፣ መግደልን፣ ማጥፋትን ታሳቢ አድርጎ ሰርቶ አያውቅም፤ -መከላከያ ሠራዊት በራሱ ተነሳሽነት ማንንም አጥቅቶ አያውቅም አሁንም ማንንም አያጠቃም፤ -የሀገር መከላከያ ሠራዊት በሀገር ውስጥ እና በአፍሪካ ብቻ ሳይሆን በኮሪያም እንዳሳየው የሰላም አስከባሪ ሆኖ ላለፉት በርካታ ዓመታት ሰርቷል፤ አሁንም የሰላም አስከባሪ ሆኖ በሀገር ውስጥና በውጭ ይሰራል፤ -ሰላም ከማስከበር፣ ሰላም ከማፅናት፣ ሰላም ከመጠበቅ፣ የሀገር ብልፅግና እንዲቀጥል ከማድረግ ውጭ የሀገር መከላከያ ሌላ ተልዕኮ የለውም፤ – ኢትዮጵያ በኃይልና በወረራ ማሳካት የምትፈልገው አንዳች ነገር የለም፤ -ለጋራ ጥቅም፣ ለጋራ እድገት፣ ለጋራ ብልፅግና ሁሉንም አሸናፊ በሚያደርጉ ጉዳዮች ከወንድሞቻችን ጋር ተወያይተን የጋራ ጥቅም የምናስከብር እንጂ በኃይል ፍላጎቶቻችንን ለማሳካት ወንድሞቻችን ላይ ቃታ የምንስብ አይደለንም፤ -ኢትዮጵያን ማፍረስ፣ የኢትዮጵያን ተቋም ማፍረስ፣ የኢትዮጵያን አብሮነትንና ወንድማማችነትን ማፍረስ፣ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ቢሆን ያልተገባ ተግባር በመሆኑ ትምህርት ልንወስድበት ይገባል፤ -ኢትዮጵያ ታሪክ ጠገብ ትልቅ ሀገር ናት፤ መከላከያ ሠራዊት ብቻ እንኳን 116 ዓመት የሚለውን ስንት ሀገር በዚህ ደረጃ ሊጠራ እንደሚችል እርግጠኛ አይደለሁም፤ -ይህንን የተከበረ ሀገር እና ተቋም ማፅናትና መጠበቅ ልዩነት ካለም በውይይት በድርድር መፍታት መለመድ ይኖርበታል፤ -ወንድም ወንድሙን እየገደለ መቀጠል የለበትም፤ -እኛ መዋጋት እናውቃለን፣ ማሸነፍ እናውቃለን እድሜያችንን በሙሉ ያሳለፍነው በዚህ ነው ነገር ግን በውጊያ ከማሸነፍ በእጅጉ የላቀው በሰላም ማሸነፍ ነው፤ -ከሰራን ሊቀየር የሚችል ሀገር እንዳለን ባለፉት ጥቂት ዓመታት መገንዘብ ችለናል፤ -ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በአምስት ዓመት ውስጥ በጦርነት፣ በኮሮና ጫና ሳትንበረከክ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት እድገቷን እጥፍ ማድረግ ችላለች፤ -አላደጋችሁም ለምትሉን የዕድገት መለኪያዎች ላልገባችሁ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በ5 ዓመት ውስጥ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት እድገቷን ደግማለች፤ -ትግላችን ይቀጥላል ማንኛውም ፈተና ከዕድገታችን፣ ከብልፅግና፣ ኢትዮጵያን ከማፅናት ሊያቆመን አይችልም፤ -እያንዳንዱን ፈተና እንማርበታለን፣ እያንዳንዱን ፈተና እንሰራበታለን፣ እያንዳንዱን ፈተና ኢትዮጵያን እናጸናበታለን፣ እያንዳንዱን ፈተና ኢትዮጵያን እንሰራበታለን፤ በታምራት ቢሻው 1,042 Share FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailViberPrint