Fana: At a Speed of Life!

ድምጻዊ አባይነህ ደጀኔ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የሰርግ ሙዚቃን በሸክላ ያስቀረጹት አንጋፋው ድምጻዊ አባይነህ ደጀኔ ድንቁ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

አርቲስት አባይነህ ደጀኔ የሰርግ ሙዚቃ ሲነሳ ስማቸው አብሮ የሚነሳ ሲሆን÷ በተለይ በ1964 ዓ.ም በሆላንድ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የሰርግ ሙዚቃን በሸክላ አስቀርጸዋል፡፡

“አንቺ ቆንጆ ጽጌረዳ የበርሃ ሎሚ” የተሰኘው ሙዚቃም ዘመን ተሻጋሪና የሚታወስ ነው፡፡

ከ1955 ጀምሮ እስከ 1983 ዓ.ም በሙዚቃው ዓለም ያሳለፉት ድምፃዊው፤ በተለይ የአየለ ማሞ (ማንዶሊን ተጫዋች) የቅርብ ጓደኛ ነበሩ።

ከአርቲስት ጥላሁን ገሰሰ፣ መሀሙድ አህመድ፣ ተፈራ ካሳ፣ እሳቱ ተሰማ፣ ብዙነሽ በቀለ፣ ተዘራ ሀይለ ሚካኤል፣ መስፍን አበበ እና ተስፋዬ ለሜሳ ጋር ጥሩ የሙዚቃ ጊዜያትን እንዳሳለፉ ታሪካቸው ያስረዳል።

በኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ከቀን ሰራተኝነት ተነስተው ላለፉት 25 ዓመታት እንዳገለገሉ፤ ለ16 ዓመታት ደግሞ በኤሌክትሪሽያንነት እንዲሁም ለ9 ዓመታት ደግሞ በሚኒ ሚዲያ ባለሙያነት እንዳገለገሉ የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል፡፡

ከአባታቸው ከአቶ ደጀኔ ድንቁና ከእናታቸው ከወ/ሮ ትርፍነሽ አንበርብር በሻሸመኔ ከተማ በ1940 ዓ.ም የተወለዱት አርቲስት አባይነህ ደጀኔ በተወለዱ በ76 ዓመታቸው በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

አርቲስት አባይነህ ደጀኔ የአምስት ወንድ ልጆች አባት ነበሩ፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.