Fana: At a Speed of Life!

የጤና ሚኒስቴር የጋራ ስትሪንግ ኮሚቴ ስብሰባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር የጋራ ስትሪንግ ኮሚቴ ስብሰባ እየተካሄደ ነው፡፡

በስብሰባው ላይ የጤና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የክልል ጤና ቢሮ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በመድረኩ ባለፈው የጋራ ስትሪንግ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ የተነሱ ውሳኔዎች ክትትል እና ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ዝርዝር ጉዳዮች መቅረባቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም የ2015 በጀት ዓመት የፋይናንስ አጠቃቀምን ጨምሮ የጤና ዘርፍ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በየዘርፉ የተሻለ አፈፃፀም መታየቱ የተገለጸ ቢሆንም በክልሎች መካከል የአፈፃፀም ልዩነቶች መታየቱ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

የጤናው ዘርፍ የመካከለኛ ጊዜ (የሦስት ዓመት ዕቅድ) የእድገትና የኢንቨስትመንት ዕቅድ እና ዕቅዱን ለማስፈፀም የሚያስፈልገው የገንዘብ ምንጭ እንዲሁም የጤናው ዘርፍ የ2016 በጀት ዕቅድ በመድረኩ ቀርቦ ውይይት እንደተደረገበት ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ የሕክምና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ሁኔታን የሚመለከት በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተደረገ ሀገራዊ የዳሰሳ ጥናትም በመድረኩ መቅረቡ ተጠቁሟል፡፡

በውይይቱም በተለይ በጤናው ዘርፍ የሚሰጡ አገልግሎት ጥራት ላይ ይበልጥ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስገንዝበዋል።

ከጥቅምት 21 እስከ 23 ቀን 2016 ዓ.ም 25ኛው ዓመታዊ የጤና ጉባዔ እንደሚካሄድም ተመላክቷል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.