የብሄራዊ አቪዬሽን አካባቢ ጥበቃ ኮሚቴ ተቋቋመ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ያካተተ የብሄራዊ አቪዬሽን አካባቢ ጥበቃ ኮሚቴ መቋቋሙን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ኮሚቴው የተቋቋመው የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ደንጌ ቦሩ እና የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው መንግስቴ በተገኙበት ነው፡፡
አቶ ደንጌ ቦሩ በዚሁ ወቅት÷ በዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት በአካባቢ ጥበቃ ላይ የወጡ ደረጃዎችን ተግባራዊ በማድርግ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ኢንዱስትሪ ላይ ተወዳዳሪ ለማደርግና አየር መንገዱ ያለበትን ደረጃ ሊመጥን የሚችል የአካባቢ ጥበቃ ለመስራት ሁሉም ኃላፊነቱን መወጣት አለበት ብለዋል፡፡
የተቋቋመው ኮሚቴ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት ተረድቶ በፍጥነት ወደ ስራ በመግባት ስራውን በዘላቂነት ማስቀጠል እንዳለበትም ማሳሰባቸውን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡