Fana: At a Speed of Life!

በኔፓል በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከ150 በላይ ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኔፓል በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከ150 በላይ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡

ርዕደ መሬቱ ከዋና ከተማዋ ካታማንዱ በ500 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኙ ጃጃርኮትና ምዕራብ ሩኩም ግዛቶች ነው የተከሰተው፡፡

የነፍስ አድን ሰራተኞች እና የጸጥታ አካላትም ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች ለመርዳትና ወደ ጤና ተቋማት ለመውሰድ በስፍራው መሰማራታቸው ተገልጿል፡፡

የኔፓል ጠቅላይ ሚኒስትር ፑሽፓ ካማል ዳሃል ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች መጎብኘታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአደጋው ችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ለማትረፍ አስፈላጊው ርብርብ እንዲደረግ አሳስበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.