ቻይና በሣይንስና ቴክኖሎጂ መስክ ፈጠራን አስመልክቶ ከተለያዩ ሀገራት ጋር ለመስራት ፍቃደኛ ናት – ፕሬዚዳንት ሺ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና በሣይንስና ቴክኖሎጂ መስክ ፈጠራን አስመልክቶ ከተለያዩ ሀገራት ጋር ለመስራት ፍቃደኛ መሆኗን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ገለጹ፡፡
ፕሬዝዳንቱ በደቡብ ምዕራብ ቻይና ቾንግቺንግ ማዘጋጃ ቤት በተከፈተው የመጀመሪያው በሣይንስና ቴክኖሎጂ ሽግግር የቤልት ኤንድ ሮድ ኮንፈረንስ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በጽሁፍ ባስተላልፉት መልዕከትም፥ ሦስተኛው የቤልት ኤንድ ሮድ ፎረም ለዓለም አቀፍ ትብብር በተሳካ ሁኔታ መካሄዱን አስታውሰዋል፡፡
ለቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ ከፍተኛ ጥራት ያለው ልማት አዲስ ምዕራፍ እንደሆነ ጠቅሰው፥ ለዚህም የሣይንስ ቴክኖሎጂ ትብብር አስፈላጊ አካል እንደሆነ አንስተዋል።
ቻይና በሰላምና የትብብር መንፈስ፣ ራስን ተደራሽ ማድረግና የመተባበር፣ የመማማርና የጋራ ተጠቃሚነትን በቤልት ኤንድ ሮድ ሣይንስ ሙሉ ለሙሉ እንዲተገበር፣ የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን የትብብር ተግባራዊነት እንዲሁም ዓለም አቀፍ የሣይንስ ቴክኖሎጂ ፈጠራ ሽግግሮችን እንደምታከናውን ገልጸዋል።
በፈጠራ ዕድገት እምቅ አቅምን ለመጠቀም፣ የፈጠራ ትብብርን ለማስፈን፣ የፈጠራ አጋርነትን ለማጠናከር፣ ሁሉም ሀገራት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የፈጠራ ውጤቶችን ለማስተዋወቅ ቻይና በጋራ ለመስራት ፍቃደኛ መሆኗንም ነው ያስታወቁት።
በዚህም ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ ከፍተኛ ጥራት ላለው ልማት እና ለሰው ልጅ የወደፊት የጋራ ተጠቃሚነት ያለው ማህበረሰብ እንዲገነባ የበኩሉን አስተዋፅዖ ማበርከቱንም ነው የጠቆሙት ፕሬዚዳንት ሺ።
“በአንድነት ለፈጠራ፣ ለሁሉም ልማት” በሚል መሪ ቃል ጉባዔው እየተካሄደ ነው፡፡
ይህን ጉባዔም ሣይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ቻይና የሣይንስ አካዳሚ፣ የቻይና ኢንጂነሪንግ አካዳሚ፣ የቻይና ሣይንስና ቴክኖሎጂ ማህበር፣ ቾንግቺንግ ማዘጋጃ ቤት ህዝቦች መንግስት እና የሲቹዋን ግዛት በጋራ አዘጋጅተውታል።
#China #BeltandRoad
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!