ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ስምንት አባላት ያሉት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ዕጩ መልማይ ኮሚቴ ሰየሙ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ስምንት አባላት ያሉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ዕጩ መልማይ ኮሚቴ ሰየሙ።
መልማይ ኮሚቴው ወደ ስራ የገባ ሲሆን በቅርቡም ጥቆማ መቀበል ይጀምራል ተብሏል።
የኢፌዴሪ ህገ መንግሥት አንቀጽ 102 እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ 1133/2011 አንቀፅ 5/1 ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዕጩ የስራ አመራር ቦርድ አባላት የሚመለምል ገለልተኛ ኮሚቴ እንደሚሰይሙ ይደነግጋል።
በዚሁ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ስምንት አባላት ያሉት የዕጩ ሰብሳቢ መልማይ ኮሚቴ የሰየሙ ሲሆን እነዚህም፦
1. ቀሲስ ታጋይ ታደለ……………….. ሰብሳቢ
2. ተከተል ዮሐንስ (ፕ/ር) ………….አባል
3. አቶ ባዩህ በዛብህ…………. አባል
4. ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) …………. አባል
5. አቶ ካሳሁን ፎሎ…………. አባል
6. ወይዘሮ ርግበ ገብረሃዋርያ…………. አባል
7. ወይዘሮ እንግዳዬ እሸቴ…………. አባል
8. መላኩ እዘዘው (ኢ/ር) …………. አባል ናቸው።
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ዕጩ መልማይ ኮሚቴው ወደ ስራ የገባ ሲሆን በቅርቡም ጥቆማ መቀበል ይጀምራል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በገዛ ፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸው ይታወሳል።