Fana: At a Speed of Life!

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከዩኔስኮ የዓለምአቀፉ የትምህርት ዕቅድ ተቋም ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በተመድ የትምህርት፣ ሳይንስ እና ባህል ድርጅት ዩኔስኮ ዓለምአቀፍ የትምህርት ዕቅድ ተቋም ጋር ተወያዩ፡፡

በፈረንሳይ ፓሪስ እየተካሄደ ካለው 42ኛው የዩኔስኮ አጠቃላይ ጉባኤ ጎን ለጎን የትምህርት ሚኒስትርና የብሔራዊ ዩኔስኮ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በዩኔስኮ ከዓለምአቀፉ የትምህርት ዕቅድ ተቋም ዳይሬክተር ማርቲን ቤናቪድሠን ጋር መወያየታቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በትምህርት ሚኒስቴር ፣ አዲስ የተዋቀሩ ክልሎች ትምህርት ቢሮዎች እና የዩኒቨርሲቲ የዕቅድ ዝግጅት ባለሙያዎችን አቅም መገንባት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ውይይት ማካሄዳቸውም ተመላክቷል፡፡

ትምህርት ሚኒስትሩ አያይዘውም በከፍተኛ ትምህርቱ ዘርፍ ያሉትን የፖሊሲ ማዕቀፎችና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማዊ ነፃነት ማረጋገጥ ላይ እየተከናወኑ ባሉ የሪፎርም ሥራዎች ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡

በዩኔስኮ የዓለምአቀፉ የትምህርት ዕቅድ ተቋም ዳይሬክተር ማርቲን ቤናቪድሰን ከኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር የበለጠ ተቀራርቦ ለመሥራት ፍላጎት ያላቸው መሆኑን አረጋግጠዋል።

በውይይቱ መጨረሻ ሁለቱ ወገኖች ያላቸውን ትብብር በማደስና በማጠናከር በትምህርቱ ዘርፍ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ለማከናወን መግባባት ላይ ደርሠዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.