Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ለአፍሪካ ሀገራት 25 ሺህ ቶን የስንዴ ድጋፍ ላከች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ለአፍሪካ ሀገራት 25 ሺህ ቶን የስንዴ ድጋፍ መላኳን የሀገሪቱ ጉምሩክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

የስንዴ ድጋፉን የጫኑ መርከቦችም በጥቁር ባህር በኩል ወደ አፍሪካ ጉዞ መጀመራቸው ነው የተገለጸው፡፡

የስንዴ አቅርቦቱ ቱርክ ከደረሰ በኋላ በሀገሪቱ በሚገኙ ዱቄት ፋብሪካዎች ተዘጋጅቶ ወደ አፍሪካ ሀገራት እንደሚሰራጭም አር ቲ ዘግቧል፡፡

ይሁን እንጂ የነጻ ስንዴ አቅርቦቱ ለየትኞቹ የአፍሪካ ሀገራት እንደሚሰራጭ በመረጃው አልተጠቀሰም፡፡

በሩሲያ ቅዱስ ፒተርስበርግ በተካሄደው የሩሲያ-አፍሪካ የኢኮኖሚ ጉባኤ ላይ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን÷ ሩሲያ ለአፍሪካ የምታደርገውን የሰብዓዊ ድጋፍ አጠናክር እንደምትቀትል መናገራቸው ይታወሳል፡፡

በዚህ ወቅትም ፕሬዚዳንት ፑቲን ለስድስት የአፍሪካ ሀገራት የምግብ እህል በነጻ ለማቅረብ ስምምነት ተፈራርመው ነበር፡፡

በፈረንጆቹ 2022 ላይ ሩሲያ 11 ነጥብ 5 ሚሊየን ቶን በላይ የምግብ እህል ወደ አፍሪካ መላኳን ዘገባው አስታውሷል።

በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት መጀመሪያ 6 ወራትም 10 ሚሊየን ቶን የምግብ እህል ለአፍሪካ ማቅረቧ ነው የተመላከተው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.