Fana: At a Speed of Life!

የግንባታ ዘርፉን አቅም የሚያጎለብቱ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የግንባታ ዘርፉን አቅም የሚያጎለብቱ ፕሮጀክቶች አስመርቋል፡፡

በምርቃት ስነ- ስርዓቱ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ(ዶ/ር)ን ጨምሮ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

ኮርፖሬሽኑ ዛሬ ለምረቃ ካበቃቸው ፕሮጀክቶች መካከል የግንባታ ባለሙያዎች ልማት ኢኒስቲትዩት ፣ የግንባታ ኢንዱስትሪዎች ግብዓት ማምረቻና ማከፋፈያ እንዲሁም ቢውልዲንግ ኢንፎርሜሽን ሞዴሊንግ ይገኙበታል ።

ከዚህ ባለፈም ኮርፖሬሽኑ ያለፈባቸውን ሂደቶች የሚያስቃኙ የፎቶግራፍ አውደ- ርዕይ ለጎብኚዎች ክፍት መደረጉም ነው የተገለጸው።

ተቋሙ በ10 ዓመቱ ከያዛቸው የልማት ፕሮግራሞች ውስጥ የግንባታ ዘርፍ አንዱ ሲሆን ፥ ዘርፉን በሰው ሃይልና ቴክኖሎጂ ተወዳዳሪ እንዲሆን እየሰራ እንደሆነ ተነስቷል።

ዛሬ ለምርቃት የበቁት ፕሮጀክቶች በመስኩ የተሻለ ስራ ለመከናወን ተጨማሪ አቅም የሚፈጥሩ መሆናቸውም ነው የተነሳው፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.