Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች ወጣቶች የኢትዮጵያን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የሚያንፁ ፕሮጀክቶች እንዲነድፉ ጥሪ አቀረቡ

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ወጣቶች የኢትዮጵያን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የሚያንፁ ፕሮጀክቶችን በመንደፍ ለሚስተዋሉ ክፍተቶች መፍትሄ በመፍጠር የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንዲወጡ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ከንቲባዋ አብርሆት ቤተ መጽሐፍት ከኤ2ኤስቪ (A2SV) ጋር በመቀናጀት ባዘጋጀው የአፍሪካ የቴክኖሎጂ ልቀትና የፈጠራ ስራን በሚያበረታታው የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ውድድር ላይ ተገኝተው ወጣቶችን አበረታተዋል።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ መድረኩ ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ወጣቶች የአፍሪካን የቴክኖሎጂ ለውጥ እውን ለማድረግ ሃሳብ የሚለዋወጡበት ፣ ተቀራርበው በጋራ የሚሰሩበት እና ለአፍሪካ ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ ለማበጀት በጋራ የሚሰሩበት መሆኑን አስፍረዋል።

ከንቲባ አዳነች “ወጣቶቻችን የኢትዮጵያን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የሚያንፁ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመንደፍ ሃገራችን ውስጥ ለሚስተዋሉ ክፍተቶች ወቅቱን የሚመጥን መፍትሄ በመፍጠር የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንዲወጡ ጥሪዬን ለማስተላለፍ እወዳለሁ” ብለዋል::

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.