Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ሰመሪታ ከዓለም አቀፉ የአረንጓዴ ልማት ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ሰመሪታ ሰዋሰው ከዓለም አቀፉ የአረንጓዴ ልማት ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዳንኤል ጎቦናያ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የሚከናወኑ ሥራዎችን በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ለአየር ንብረት ለውጥ ሥራዎች የሚውል ገንዘብ ማግኘት በሚቻልባቸው አዳዲስ የፈጠራ መንገዶች ላይ ተወያይተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የጀመረችው የአረንጓዴ አሻራ ልማት ግቡን እንዲመታ የሚያስችል አቅም ለመገንባት በትኩረት መስራት እንደሚገባ ዳይሬክተሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

በአየር ንበረት ለውጥ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ባለው ሥራ ደስተኛ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.