Fana: At a Speed of Life!

የግልገል በለስ-ድኋንዝ ባጉና-ድባጤ መንገድ ዳግም አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጸጥታ ችግር ለዓመታት ተቋርጦ የቆየው የግልገል በለስ-ድኋንዝ ባጉና-ድባጤ መንገድ ዳግም አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የመተከል ዞን አስታውቋል፡፡

መንገዱ በማንዱራ ወረዳ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የጉህዴን ታጣቂዎች የሰላም ስምምነት ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው ዳግም አገልግሎት መስጠት የጀመረው፡፡

መንገዱን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ፣ የማንዱራ፣ የድባጤ፣ የዳንጉርና የማንዱራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪዎች ጨምሮ የሰላም ተመላሾች ተወካዮችና የጸጥታ አካላት በይፋ አስጀምረዋል፡፡

የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ለሜሳ ዋውያ÷ በማንዱራ ወረዳ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የጉህዴን ታጣቂዎች የሰላም ስምምነት ማድረጋቸውን ተከትሎ መንገዱ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልጸዋል።

በትናንትናው ዕለት የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ለዓመታት ዝግ ሆኖ የቆየው የትራንስፖርት አገልግሎት መከፈቱ በህብረተሰቡ ላይ ሲደርስ የነበረውን ጫና ይቀርፋል ብለዋል።

ከፍተኛ አመራሮች እና የሀገር ሽማግሌዎች በቀጠናው ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ከሰላም ተመላሾች ጋር ባደረጉት ከፍተኛ ውይይት መንገዱ ክፍት ተደርጓል ነው ያሉት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.