Fana: At a Speed of Life!

የሀዋሳ ከተማ ለህዳሴ ግድብ ዋንጫ 27 ሚሊየን ብር መሰብሰቡ ተገለፀ

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ መድረክ በሲዳማ ብሔራዊ ክልል በሐዋሳ ከተማ ዛሬ ተካሄዷል።

የግድቡ ዋንጫ በከተማዋ በነበረው የሶስት ቀናት የገቢ ማሰባሰቢያ ቆይታ 27 ሚሊየን ብር ማሰባሰብ መቻሉን የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ መኩሪያ ማርሻዬ በገቢ ማሰባሰቢያ መድረኩ ላይ ገልፀዋል።

ለግድቡ ግንባታ በሲዳማ ክልል ደረጃ እስካሁን በተደረገ የገቢ ማሰባሰብ ስራ ከ756 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የክልሉ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ክፍሌ ሀሜሶ ተናግረዋል።

ግድቡ ወደ ክልሉ ከገባበት ከህዳር 29 ቀን 2015 ዓም ጀምሮ መላው ህዝቡ ባለው አቅም ሁሉ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል ያሉት አቶ ክፍሌ፤ የገቢ ማሰባሰብ ስራው በሁሉም የክልሉ ዞኖችና ከተማዎች እስከ ህዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም ጠቁመዋል።

በመጨረሻም ዋንጫው በቀጣይ ወደሚጓዝበት በሲዳማ ብሔራዊ ክልል የሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፊሊጶስ ናሆም ከሐዋሳ ከተማ ዋንጫውን በክብር ተረክበዋል።

 

በመሪያማ በቀለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.