Fana: At a Speed of Life!

የኖርዲክ ብላክ የሙዚቃና ቴአትር ቡድን አባላት ስራዎቻቸውን በኢትዮጵያ ሊያቀርቡ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 28 አባላትን የያዘው የኖርዲክ ብላክ የሙዚቃና የቴአትር ቡድን በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብቷል።

ለልዑካኑ ቡድኑ የቱሪዝም ሚኒስቴር አቀባበል ያደረገላቸው ሲሆን ሚኒስትሯ ናሲሴ ጫሊ በዚህ ወቅት፥ የቡድኑ አባላትና አርቲስቶች ወደ ኢትዮጵያ መምጣት በኖርዌይ እና በኢትዮጵያ መካከል የባህል ልውውጥን ለማጠናከር የሚረዳ ነው ብለዋል።

እንዲሁም የኢትዮጵያን የቱሪዝምና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ለማስተዋወቅ ትልቅ ዕድል ይኖረዋልም ነው ያሉት።

የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ሌንሳ መኮንን በበኩላቸው ፥ መሰል መርሐ-ግብሮችን ማዘጋጀት የኢትዮጵያን የቱሪዝም ሃብት ለማስተዋወቅ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ገልጸዋል።

ልዑካኑ የ10 ቀናት ቆይታ የሚኖራቸው ሲሆን፥ በቆይታቸው በአሊያንስ፣ በብሄራዊ ቴአትር፣ በኢትዮ- ፍራንስ እና በአፍሪካ ህብረት የማያ አንጄሎ የህይወት ታሪክ ላይ የሚያተኩር ሙዚቃዊ ተውኔት ያቀርባሉ ተብሏል።

በተጨማሪም የልዑካን ቡድኑ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን የሚጎበኝ ሲሆን ፥እነዚህን መዳረሻዎች በሚዘዋወሩባቸው ሀገራት ሁሉ እንዲያስተዋውቁ የአምባሳደርነት ሚና ይሰጣቸዋል ተብሏል።

የሙዚቃ እና ተውኔት ባለሙያዎቹ ይዘዋቸው የመጡትን የሙዚቃ መሳሪያዎች እና የቴአትር መድረክ ግብዓቶችን በስጦታ መልክ ለብሔራዊ ቴአትር እንደሚያበረክቱም ይጠበቃል።

በመራኦል ከድ

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.