Fana: At a Speed of Life!

ጠላቶቻችን እርስ በርስ ለማጋጨት የሚያደርጉትን ሴራ ማክሸፍ ያስፈልጋል- ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውስጥና የውጭ ጠላቶቻችን እርስ በርስ ለማጋጨት የሚያደርጉትን ሴራ ማክሸፍ እና የተሠለፉበትን ሠራዊቱን የማጥላላት የውሸት ዘመቻ መመከት እንደሚገባ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ፡፡

የመከላከያ ሠራዊት የክብር አባላት ለፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የምስጋና ሽልማት አበርክተዋል፡፡

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ለተበረከተላቸው ሽልማት አመስግነው÷ ለትውልድ የሚተላለፍ ታሪክ ነው ያበረከታችሁት ብለዋል፡፡

እናንተ ሀገር ወዳዶችን የክብር አባል በማድረጋችን በጣም ደስተኞች ነን፤ ወደፊትም ለሀገራችሁ፣ ለሕዝባችሁ፣ እና ለሠራዊቱ የምታደርጉትን በጎ ተግባር አጠናክራችሁ ቀጥሉ ማለታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከክብር አባላቱ ጋር በሕግ የተቀመጠውን እየተገበርን በጋራ ለመሥራት ዝግጁ ነን ሲሉም አረጋግጠዋል፡፡

የውስጥና የውጭ ጠላቶቻችን እርስ በርስ ለማጋጨት የሚያደርጉትን ሴራ ማክሸፍ እና የተሠለፉበትን ሠራዊቱን የማጥላላት የውሸት ዘመቻ መመከትና እውነታውን መግለፅ እንደሚያሥፈልግም ነው ያስገነዘቡት፡፡

የክብር አባላቱን በመወከል ስጦታውን ያበረከቱት ሚስባህ ከድር በበኩላቸው÷ በየግላችን በነበረን እንቅስቃሴ ይህ የሀገራችን ታላቅ ተቋም ሥራችንን አይቶና መርጦ የክብር አባላት ስላደረገን እናመሰግናለን ነው ያሉት፡፡

ለዚህ ምስጋናችንም በወታደራዊ ሙዝየም የሚቀመጥ ስጦታ አበርክተናል ብለዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.