Fana: At a Speed of Life!

የዓየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሴቶችን ውሳኔ ሰጭነት ማሳደግ እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሴቶችን ውሳኔ ሰጭነት ማሳደግ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምሥጋኑ አርጋ ገለጹ፡፡

በመጪው የፈረንጆቹ ታሕሣሥ ወር በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች በሚካሄደውን 28ኛው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ዙሪያ ያተኮረ ውይይት በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

አምባሳደር ምሥጋኑ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷የሴቶችን የውሳኔ ሰጭነት ሚና በማሳደግ ያላቸውን ጥበብና የፈጠራ ክኅሎት የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም በሚደረገው ጥረት መጠቀም ያስችላል ቁልፍ ሚናም ይጫወታል።

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ÷ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአየረንጓዴ ልማት ብሔራዊ የመቋቋሚያ ዕቅድ አውጥታ እየተገበረች መሆኑንም ገልፀዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ወሳኝ ርምጃ በመውሰድ ምድራችን ከአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ በመታደግ ለቀጣዩ ትውልድ ብሩህ ተስፋን ማስረከብ ይገባናል ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.