Fana: At a Speed of Life!

ከ28 ሺህ በላይ ሀሰተኛ የአሜሪካ ዶላር ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ28 ሺህ በላይ ሀሰተኛ የአሜሪካ ዶላር ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረው ግለሰብ ተይዞ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
 
ተጠርጣሪው በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2- C 32496 አ/አ በሆነ ተሽከርካሪ ውስጥ 284 ባለ መቶ ኖቶች (28 ሺህ 400) ሀሰተኛ የአሜሪካ ዶላር ይዞ ሲንቀሳቀስ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 መክሊት ህንፃ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በቁጥጥር ስር ውሏል።
 
በተሽከርካሪው ውስጥ በተደረገ ፍተሻ ከሃሰተኛ ዶላሩ በተጨማሪ ስታር ሽጉጥ ከስምንት ጥይቶች ጋር ተይዞ ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
ሀሰተኛ ገንዘቦችን በማተምና ወደ ገበያ ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ የሚፈፀም ወንጀል በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጫና እንደሚያሳድር ፖሊስ አስገንዝቧል፡፡
 
በመሆኑ ይህንን ህገ ወጥ ተግባር የሚፈፅሙ ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ህብረተሰቡ ለፀጥታ አካላት የሚሰጠውን መረጃና ጥቆማ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል።
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.