የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን 1 ሺህ 585 ፍቃዶችን ሰጠ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን በንግድ ምልክት፣ በፓተንት፣ የቅጅና ተዛማጅ መብቶችን ጨምሮ በአጠቃላይ 1 ሺህ 585 ፍቃዶችን ሰጠ።
የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የደንበኞች አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ ኤልያስ ጥሩነህ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ ተቋሙ ፈቃዱን የሰጠው በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያ አራት ወራት ውስጥ ነው።
በዚህም ንግድ ምልክት፣ ፓተንት ፍቃድና ኢንዱስትሪያል ዲዛይንን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ፍቃድ መሰጠቱን ገልጸዋል።
በተለይም ፍቃድ ከተሰጣቸው ዘርፎች መካከል በንግድ ምልክት ብቻ 1 ሺህ 8 ፍቃዶች ተሰጥተዋል።
በተጨማሪም 16 በፓተንት ፍቃድ፥ 102 በአገልግሎት ሞዴል እንዲሁም 65 በኢንዱስትሪያል ዲዛይን ፍቃድ መስጠቱን ተናግረዋል።
በተለይም ተቋሙ በአስገቢ ፓተንት 20 ፍቃድ የሰጠ ሲሆን፥ በቅጅና ተዛማጅ መብቶች ደግሞ 374 ፍቃዶችን ሰጥቷል።
በሌላ በኩል ተቋሙ በተመዘገቡ የአእምሯዊ ፈጠራ መብቶች ላይ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የመብት ጥሰት እንዳይፈጸም በተጠናከረ መልኩ እየተሰራ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡
በታሪክ አዱኛ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!