Fana: At a Speed of Life!

በስልጠና የተገኙ ልምዶችን በተግባር ማረጋገጥ ከአመራሩ የሚጠበቅ ቀዳሚ ጉዳይ ነው – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በስልጠናዎች የተገኙ ልምዶችን በተግባር ማረጋገጥ ከአመራሩ የሚጠበቅ ቀዳሚ ጉዳይ ነው ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ገለጹ፡፡

አቶ አደም ፋራህ÷ በመቱ ከተማ ለመንግስት አመራሮች እየተሰጠ የሚገኘውን የስልጠና ሒደት እና የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸው የሰልጣኞች ማደሪያ፣ መወያያ ክፍሎችን፣ የሕክምና መስጫና መመገቢያ ስፍራዎችን የተመለከቱ ሲሆን÷ ከሰልጣኞች ጋርም ተወያይተዋል፡፡

በቀጣይ መሰል ለአመራሩ የሚሰጡ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አቶ አደም ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ በፊት በተዘጋጁ ስልጠናዎች የተገኙ ልምዶችን በተግባር ማረጋገጥ ከአመራሩ የሚጠበቅ ቀዳሚ ጉዳይ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

በተመሳሳይ አቶ አደም በዞኑ የሚገኘውን ማረሚያ ቤት መጎብኘታቸውንም የፓርቲው መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚህም በማረሚያ ቤቱ በሰብዓዊ መብት አጠባበቅና አያያዝ፣ በታራሚዎች ክህሎት ግንባታ፣ በሃብት ማስተዳደር እና ሌሎች ስራዎች እየተከናወኑ እንደሆነ መመልከታቸውን ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.