ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቤልጅየም ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 21 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቤልጅየም ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ዴ ክሮ ጋር ተወያዩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኮፕ28 ጉባኤ አስቀድሞ መወያየታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።
በውይይታቸውም በወቅታዊ የሀገር ውስጥ እና ሁለትዮሽ ትብብር ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
ከውይይቱ ባለፈም በኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ መካነ ርዕይ/ፓቪሊዮን/ ተገናኝተው ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋምና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የምታደርገውን ጥረትና ያላት ቁርጠኝነት የሚያሳየውን አውደ ርዕይ ጎብኝተዋል።