የቴክኒክና ሙያ ዘርፍን ውጤታማ ለማድረግ የመገናኛ ብዙኃን የበኩላቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቴክኒክና ሙያ ዘርፍን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የመገናኛ ብዙኃን ዘርፉን በማስተዋወቅና ማኅበረሰቡን ስለ ዘርፉ በማስገንዘብ የበኩላቸውን እንዲወጡ የሥራና ክኅሎት ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ።
ሚኒስቴሩ በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ላይ ያተኮረ “ክኅሎት ለሁለንተናዊ ስኬት” በሚል መሪ ሀሳብ የግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት መድረክ ከመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ኃላፊዎች ጋር አካሂዷል።
የሥራና ክኅሎት ሚንስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት÷ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት በክኅሎት ዘርፍ የሚታዩ የተዛቡ ሐሳቦችን በማስተካከልና ለወጣቶች ግንዛቤ በመስጠት የድርሻውን ሊወጣ ይገባል።
በክኅሎት ዘርፍ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ጋር ለመድረስ መገናኛ ብዙኃን ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸው÷ ሠርቶ መለወጥን የሚችል ማኅበረሰብ ለመገንባት የጋራ ርብርብ እንደሚጠይቅ አብራርተዋል።
ዘርፉ ምርታማነትን ማረጋገጥ የሚያስችሉና ባለ ብሩኅ አዕምሮ ዜጎች የሚፈሩበት በመሆኑ÷ ይህንን እውነት የሚገልጡ ሥራዎች ከመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ይጠበቃል ነው ያሉት።
የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ የሥራ ባህሉ የዳበረ ማኅበረሰብ በመፍጠር የበለፀገች ኢትዮጵያን ለማየትና ለሥራና ክኅሎት ልዩ ትኩረት በመስጠት በጋራ መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!