Fana: At a Speed of Life!

ከ2 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተገነቡ የሚገኙ ፕሮጀክቶች ተጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ከ2 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በአዲስ አበባ እየተገነቡ የሚገኙ የጤና ማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ።

በጉብኝቱ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባዔ ሎሚ በዶን ጨምሮ ሌሎች የምክር ቤት አባላትና የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ፕሮጀክቶቹ በጤና ሚኒስቴር ሥር ባሉ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ሆስፒታሎች እየተገነቡ ይገኛል።

ዶክተር ሊያ ታደሰ ፕሮጀክቶቹን አስመልክተው ለምክር ቤቱ አባላት ባደረጉት ገለጻ÷ ፕሮጀክቶቹ 2 ቢሊየን ብር በጀት እንደተያዘላቸው እና ከ 1 ሺህ በላይ አልጋዎች በውስጣቸው እንደሚይዙ አብራርተዋል፡፡

በግንባታ ላይ የሚገኙት ፕሮጀክቶችም÷ የልብ፣ የካንሰርና ሌሎች የሕክምና አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ናቸው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የፕሮጀክቶቹ ግንባታ ሲጠናቀቅም÷ በጤና ዘርፍ በተለይም ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች የሕክምና አገልግሎት መሻሻል ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጉብኝት ዓላማ ፕሮጀክቶቹ ያሉበትን ሁኔታ በመመልከት አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ መሆኑ ተመላክቷል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.