Fana: At a Speed of Life!

ኮርፖሬሽኑ ለአማራ ክልል 75 ትራክተሮችን ሊያስረክብ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 28 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን ለአማራ ክልል 75 ትራክተሮችን ላስረክብ ነው አለ።
 
የኮርፖሬሽኑ የእርሻ ዘርፍ አቅርቦትና የሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ ስራ አስፈጻሚ አቶ መንግስቱ ክፍሌ ትራክተሮቹን ለማስረከብ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።
 
ትራክተሮቹ ከውጭ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ሲሆን ለአገልግሎት ብቁ እንዲሆኑ የሙያ ስልጠና ለኦፕሬተሮች እየተሰጠ ነው ብለዋል።
 
እነዚህ ትራክተሮች የአርሶ አደሮችን አሰራር ወደ ዘመናዊ መንገድ በመቀየር ምርታማነትን የሚያሳድጉና የአርሶ አደሩን ጉልበት የሚቆጥቡ መሆናቸውንም አስረድተዋል።
 
ኮርፖሬሽኑ ዘመናዊ የሆኑ የእርሻ መሳሪያዎችን ለአርሶ አደሩ በማቅረብ ግብርናውን ለማዘመን በትኩረት እንደሚሰራም ገልጸዋል።
 
 
በሲሳይ ዱላ
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.