በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስተባባሪነት በአሶሳ ከተማ የተሰሩ ቤቶች እና የመማሪያ ክፍሎች ለማህበረሰቡ ተላለፉ
አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 30 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስተባባሪነት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ በበጎ ፈቃድ መርሐ ግብር የተሰሩ ቤቶች እና ትምህርት ቤቶች ለማህበረሰኑ ተላልፈዋል።
ትምህርት ቤቱ የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ አካል የሆነው በአሶሳ ዞን ኡራ ወረዳ የሚገኘው አቡሻ ትምህርት ቤት የመማሪያ ክፍሎች እና ቤተ መጽሐፍት ናቸው።
በርክክብ ሥነ ስርዓቱ ላይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሀላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ወይዘሮ ዓለምፀሐይ ጳውሎስ እንዲሁም የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ሃይሌ (ዶ/ር) መገኘታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።