18ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በዓል በፕሪቶሪያ ተከበረ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 18ኛው ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በዓል በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ከተማ ተከብሯል።
በበዓሉ አከባበር ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያን ፣ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አደረጃጀቶች፣ የሐይማኖት ተወካዮች፣ ሸማግሌዎች እንዲሁም ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል።
በበዓሉ ላይ የተገኙ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አማካሪ ሚኒስትር አቶ መለሰ ዓለሙ፥ ህብረታችንና አንድነታችንን አጠናክረን ጠንካራ ሀገር መገንባት ለእኛም ሆነ ለትውልዱ ዋስትና ነው ብለዋል።
ለዚህ ደግሞ ህብረ-ብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት ግንባታን በአግባቡ ማስከሄድ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
በሌላ በኩል የዜጎች ብርታትና ጥንካሬ በየመስኩ ሊጎላ እንደሚገባና ኢትዮጵያን በተቻለ መስክና አቅም መደገፍ አስፈላጊ መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል።
እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሙክታር ከድር (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ ብዝሃነትን በአግባቡ ማስተናገድ እና መምራት ለሀገራዊ አንድነት መሠረት መሆኑን አስረድተዋል።
“ብዝሃነታችን ደግሞ ዘላቅ ዋስትና የሚያገኘው የበለፀገች ጠንካራ ሀገራዊ አንድነት መገንባት ስንችል በመሆኑ ከመቼውም ጊዜ በላይ ህብረታችንና አንድነታች ልጠናከር ይገባል” ብለዋል።
በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት አንድነታቸውን አጠናክረው ለዛ የሚመጥን ጠንካራ አደረጃጀት ሊኖራቸው እንደሚገባ ማስገንዘባቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡