Fana: At a Speed of Life!

ወደ ክልሉ ከ203 ሺህ በላይ ኩንታል ማዳበሪያ እየገባ መሆኑ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ2016 /17 ዓ.ም የምርት ዘመን የሚውል ከ203 ሺህ በላይ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ መግባት መጀመሩን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ባበክር ሃሊፋ ገለጹ፡፡

በምርት ግብዓት አቅርቦት ላይ ትኩረቱን አድርጎ ዛሬ በአሶሳ ከተማ በተካሄደው ውይይት ላይ የቢሮው ኃላፊ እንደገለጹት ÷ የግብዓት አቅርቦትን ፍትሐዊ ለማድረግ የሚያስችል የሥርጭት፣ የሽያጭና የአጠቃቀም መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ትግባራ ተገብቷል፡፡

መመሪያው ክፍያ ቀድመው ለሚፈጽሙ አርሶ አደሮችና ባለሃብቶች ማዳበሪያው ፈጥኖ እንዲያገኙም ያደርጋቸዋል፡፡

በዚሁ መሠረትም ለመጪው የመኸር እርሻ አገልግሎት የሚውል ዩሪያና ዳፕ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ክልሉ መግባት ጀምሯል ነው የተባለው።

መግባት የጀመረው ማዳበሪያም በ2015/16 የምርት ዘመን ጥቅም ላይ ከዋለው በ94ሺህ ኩንታል ብልጫ አለው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በክልሉ ባለፈው ዓመት ለምርት ግብዓቶች ከተሰራጨው 505 ሚሊየን ብር እስካሁን 131ሚሊየን ብር እንዳልተከፈለ አስታውሰው÷ ለትራክተሮች ከተሰጠው ብድርም 18 ሚሊየን ብር ወቅቱን ጠብቆ አለመመለሱንም ነው ያስረዱት፡፡

ብድሩ በወቅቱ ባለመመለሱ በሌሎች የልማት እንቅስቃሴዎች ላይ ጫና እያሳደረ በመሆኑም የወረዳ አስተዳደርና የሚመለከታቸው አካላት ብድሩን በአፋጣኝ ተከታትለው እንዲመለስ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.