Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ ለቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የሚሰጠውን ዝቅተኛ አመለካከት መቅረፍ እንደሚገባ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል ለቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ የሚሰጠውን ዝቅተኛ አመለካከት ለመቅረፍ ግንዛቤ ላይ የበለጠ መስራት እንደሚገባ የክልሉ የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ አስታወቀ።
 
ክልል አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የንቅናቄ መድረክ በሲዳማ ክልል በመካሄድ ላይ ይገኛል።
 
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ ዜጎች በሚያገኙት እውቀት ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች የሚተርፉበት አቅም እንደሚፈጥርላቸው የሲዳማ ክልል የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሀገረፅዮን አበበ ተናግረዋል።
 
ክልል አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የንቅናቄ መድረክ መካሄዱም በአመራሩም ሆነ በህዝቡ ውስጥ የሚስተዋለውን የግንዛቤ እጥረት ችግር ለመቅረፍና ያለመ ነው ብለዋል።
 
በሌላ መልኩ ዘርፉ ለሀገራችን እድገት ወሳኝ መሆኑን በመግለፅ ዘርፉም የሰለጠነ የሰው ሀይል ለመፍጠር ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው አመላክተዋል፡፡
 
በሁሉም ከተማ አስተዳደሮችና ወረዳዎች እስከ ቀበሌ ድረስ እየተደረገ ባለው የውውይት መድረክ ያለውን የተማሪዎች የቅበላ መጠን ከፍ ለማድረግም እድል እንደሚፈጥር አመላክተዋል።
 
በክልሉ በዚህ ዓመት ከ20 ሺህ በላይ በመደበኛ መርሐ ግብር እንዲሁም በአጫጭር ስልጠና ከ60 ሺህ በላይ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማሰልጠን መታቀዱንም ገልፀዋል፡፡
 
ተማሪዎች በፈለጉት የትምህርት ዘርፍ በቂ እውቀት እንዲያኙ በማድረግ ስራን መፍጠር የሚችሉ እንዲሆኑ በየተቋማቱ በቂ ዝግጅት መደረጉንም ነው የተናገሩት።
 
የተቋማት አቅም ከማሽነሪዎች አቅርቦትና መሰል ግብዓቶችን ከማሟላትና ቴክኖሎጂ ከማጠቀም አንፃር ክልሉ በዚህም ዓመት ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የመማሪያ ግብዓቶችን ለመግዛት መታቀዱን ጠቅሰዋል።
 
በብርሃኑ በጋሻው
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.