Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ አየር ኃይል የእውቅና እና የምስጋና ፕሮግራም ተከናወነ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 5 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመርሐ ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት፣ ለመከላከያ የጦር ክፍሎች እና ለልዩ ልዩ የመከላከያ ስታፍ ክፍሎች ስጦታ አበርክተዋል።
 
በስጦታ መርሐ ግብሩ 88ኛውን የአየር ኃይል የምስረታ በዓል ለማክበር ኢትዮጵያ ለገቡት ለተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች አየር ኃይል አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ኢብራሂም ናስር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ምስጋና አቅርበዋል።
 
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ እንደተናገሩት የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች አየር ኃይል አባላት ከኢትዮጵያ አየር ኃይል ጋር በጋራ ሆነው የሚያቀርቡት የአየር ላይ ትርኢት ከፍተኛ ልምድና ተሞክሮ የምናገኝበት ነው።
 
የምናከብረው በአል የአየር ኃይልን ገፅታ ከማሳየት ባለፈ የህዝብ አለኝታ መሆናችንን የምናረጋግጥበት ነው ማለታቸውን የመከላከያ ሰራዊት ገጽ መረጃ ያመላክታል።
 
ነገ በሚከበረው የዓየር ኃይል ቀን ጥቁር አንበሳ በሚል ስያሜ የአየር ላይ ትርኢቶችን የኢትዮጵያ አየር ኃይል አብራሪዎች ከተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች አብራሪዎች ጋር ተቀናጅተው እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል።
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.