Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳለፈ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 6 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳለፈ።
ካቢኔው በ3ኛ አመት 7ኛ መደበኛ ስብሰባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት አስተዳደር፣ አገልግሎት አሰጣጥ፣ የሰው ኃይል እና የአሰራር ጥልቅ ሪፎርም መተግበሪያ ረቂቅ ደንብ ላይ መክሮ ውሳኔ አሳልፏል።
ውድ እና ውስን የሆነውን የከተማዋን መሬት ለማስተዳደር እና የከዚህ በፊት የአሰራር ችግሮችን በተደራጁ እና ብቁ በሆነ ሙያተኛ ሊያደራጁ የሚችሉ፣ ዘመናዊ የአሰራር ዘዴን በሚያሳልጡ እና ብልሹ አሰራርን ሊከላከሉ የሚችሉ የህግ ማዕቀፎችን መርምሮ በማፅደቅ እና ትግበራው በጠንካራ ሥነ ምግባር እንዲመራ ውሳኔ አሳልፏል።
በሌላ በኩል የአብርሆት ቤተ መፅሐፍት እና የጥቁር ህዝቦች ድል የሆነው የአድዋ ዐዐ ኪሎ ሜትር ሙዚየም ፕሮጀክት በአንድ የህግ ማዕቀፍ ማስተዳደር የሚቻልበትን ረቂቅ ደንብ መርምሮ በሙሉ ድምፅ ማጽደቁን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.