በተያዘው የምርት ዘመን 117 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ እየተሰራ ነው ተባለ On Dec 16, 2023 149 አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 6 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በተያዘው የምርት ዘመን 3 ሚሊየን ሄክታር መሬት በመስኖ በማልማት 117 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ። በሁለተኛው ምዕራፍ የግብርና ዕድገት ፕሮግራም የበጀት ድጋፍ ለመስኖ ስንዴ ልማት ለክልሎች የተገዙ የውሃ ፓምፖች የርክክብ ሥነ-ስርዓት ተካሄዷል። በዚሀ ወቅት የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ÷የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የግብርናውን ዘርፍ ከሚደግፉ የልማት አጋር አካላት ጋር በመሆን በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል። ባለፉት አምስት ዓመታት በመስኖ ስንዴ ልማት አበረታች ውጤት መመዝገቡን የገለጹት ሚኒስትሩ በተያዘው የምርት ዘመን 3 ሚሊየን ሄክታር መሬት በመስኖ በማልማት 117 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የዓለም ባንክ የግብርናውን ዘርፍ ምርታማነት ለማሳደግ ለሚያደርርገው ሁለንተናዊ ፍጋፍ ሚኒስትሩ ምስጋና አቅርበዋል። የግብርና ሚኒስቴር የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ሚኒስትር ዴኤታ መለስ መኮንን (ዶ/ር)÷ የግብርና ሚኒስቴር የ10 ዓመት ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ስራ የገባ መሆኑን እና ይህንን ግብ ለማሳካት የሚረዱ ኢኒሼቲቮችን በመቅረጽ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል። ከእነዚህ ኢኒሼቲቮች መካከል የመስኖ ስንዴ ልማት አንዱ እንደሆነ መናገራቸውን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ 149 Share FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailViberPrint