Fana: At a Speed of Life!

ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቅርቡ አጀንዳ ወደ መለየት ስራ እንደሚገባ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቅርቡ አጀንዳ ወደ መለየት ስራ እንደሚገባ አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ ዛሬ በፅህፈት ቤቱ በሰጠዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ፤ የተሳታፊ ልየታ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ያለ ሲሆን በቅርቡ አጀንዳ ወደመለየት ስራ እንደሚገባ ገልጿል።
ከዚህ ቀደም ከዳያስፖራ ማህበረሰብ፣ ከማህበረሰብ መሪዎች፣ ከማዲያ አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ስኬታማ ዉይይት መደረጉን ኮሚሽኑ አስታዉቋል።
ከአማራና ከትግራይ ክልሎች በስተቀር በሁሉም አካባቢዎች ባሉ 700 ወረዳዎች የተሳታፊ ልየታ እና ወኪሎቻቸዉን የመምረጥ ሂደት መከናወኑ ተገልጿል፡፡
በአማራና በትግራይ ክልሎች በጦርነትና በልዩ ልዩ ችግሮች ምክንያት የተሳታፊ ልየታ ማድረግ እንዳልተቻለ በመግለጫዉ ተነስቷል፡፡
ነገር ግን በክልሎቹ ባሉ አካባቢዎች ላይ የተሳታፊ ልየታ ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተመላክቷል።
በምንተስኖት ሙሉጌታ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.