Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ቀጣና ያላት ስትራቴጂካዊ ፍላጎት ላይ ያተኮረ አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ቀጣና ያላት ስትራቴጂካዊ ፍላጎት ላይ ያተኮረ ሀገር አቀፍ አውደ ጥናት ዛሬ በሰመራ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው፡፡
አውደ ጥናቱን ያዘጋጁት÷ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ከአዲስ አበባ፣ መቀሌ፣ ድሬዳዋ እና ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር መሆኑ ተገልጿል፡፡
በአውደ ጥናቱ ላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ቀጣና ላይ ያላትን ስትራቴጂካዊ ፍላጎት በሚመለከት ጥናታዊ ጽሑፎች እንደሚያቀርቡ ተጠቁሟል።
ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ላይ ያላትን ስትራቴጂካዊ ፍላጎት ከታሪካዊ አውዱ አንጻር የሚቃኝ እንዲሁም ከጂኦ ፖለቲካና ዓለም አቀፍ ሕግ አንጻር የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት ተሞክሮ የሚዳሰስባቸው ጥናታዊ ጽሑፎችም ይቀርባሉ ተብሏል።
በተጨማሪም የቀይ ባሕር ቀጣናን ከፉክክር ይልቅ የትብብርና የጋራ ተጠቃሚነት አካባቢ ከማድረግ አኳያ ያሉ ዕድሎች ላይ ያተኮረ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በአውደጥናቱ ላይ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች፣ ተመራማሪዎች፣ የመንግስት አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.