Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ስዊዘርላንድ 6ኛውን የጋራ የፖለቲካ ምክክር አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው የኢትዮ-ስዊዘርላንድ የጋራ የፖለቲካ ምክክር በበርን ከተማ ተካሂዷል፡፡
የሁለትዮሽ ምክክር መድረኩን የመሩት÷ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ እና የስዊዘርላንድ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የአፍሪካ ክፍል ኃላፊ አምባሳደር ፊሊፕ ስታልደር ናቸው፡፡
የምክክሩ ዓላማ የሁለቱን ሀገራት የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነት በይበልጥ ለማሣደግ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን÷ መድረኩም አህጉራዊ እና የባለብዙ ወገን የጋራ ጉዳዮችን ያካተተ ነው ተብሏል፡፡
በሁለትዮሽ ግንኙነት ላይም ሐሳብ መለዋወጥ መቻሉን እና በአዳዲስ የትብብር መስኮች ላይ ምክክር መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
የሁለቱን ሀገራት የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት በይበልጥ ለማሣደግ መስማማታቸውም ተጠቅሷል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.