የጋዜጠኛ ዓይናለም ባልቻ ሥርዓተ-ቀብር ተፈጸመ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለ25 ዓመታት ያገለገለችው ጋዜጠኛ ዓይናለም ባልቻ ሥርዓተ-ቀብር ዛሬ በቤተል ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡
ጋዜጠኛዋ በጣቢያው በልጆች ፕሮግራም ብቻ ለ15 ዓመታት ያገለገለች ሲሆን÷ በ55 ዓመቷም ትናንት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡
በጤና እክል ምክንያት ከሥራዋ ተገልላ በሕመም ላይ የነበረችው ጋዜጠኛ ዓይናለም÷ የአንዲት ሴት ልጅ እናት እና የሁለት የልጅ ልጆች አያት መሆኗ ይታወቃል፡፡
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በጋዜጠኛ ዓይናለም ባልቻ ኅልፈት የተሰማውን ኀዘን እየገለጸ÷ ለቤተሰብ እና ወዳጅ ዘመድ መጽናናትን ይመኛል።