ባለፈው ክረምት ከተተከሉ ችግኞች 85 በመቶ ያህሉ መጽደቃቸው ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 ዓ.ም በክረምት ወቅት ከተተከሉት 7 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኞች ውስጥ 85 በመቶ ያህሉ መፅደቃቸውን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በ2015 ዓ.ም የክረምት ወቅት ከተተከሉት መካከልም 57 በመቶ ለጥምር ደን እና የፍራፍሬ ችግኞች ቀሪው ደግሞ ለአካባቢ ጥበቃና ተፋሰስ ልማት የሚውሉ መሆናቸውን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
የተተከሉ ችግኞችን የፅድቀት መጠናቸውን ለማረጋገጥም የአሰሳ ሥራ በዓመት ሁለት ጊዜ እንደሚከናወን አስታውቀዋል፡፡
በቀጣይም የእንክብካቤ ተግባራትን ያለማቋረጥ በማከናወን የፅድቀት መጠኑን ከፍ የማድረግ ሥራ እንደሚከናወን ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡
እንዲሁም በመጪው የክረምት ወቅት የሚተከሉ ችግኞችን የማዘጋጀት ተግባር መጀመሩን ገልጸው÷ 9 ቢሊየን ችግኞችን ለማዘጋጀት ከክልሎች ጋር መግባባት ላይ ተደርሷል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በሁለት ምዕራፎች 50 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ዕቅድ ይዛ እየሠራች መሆኗን ገልጸው÷ በመጀመሪያው እንዲሁም በሁለተኛው ምዕራፍ የመጀመሪያ ዓመት በአጠቃላይ 32 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኞች መተከላቸውን አስታውቀዋል፡፡
በመጪዎቹ ሦስት ዓመታትም 17 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኞችን መትከል እንደሚጠበቅባትም ነው ያመላከቱት፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!