ለሀገራዊ ምክክር ስራዎች በቂ የሚዲያ ሽፋን ሊሰጥ ይገባል – አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሚያከናውናቸው ተግባራት ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲፈጠር ተገቢው የሚዲያ ሽፋን መሰጠት እንዳለበት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ገለጹ።
አፈ ጉባዔው ይህንን የገለጹት በምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የስራ አፈፃፀምን በተመለከተ ያደረገውን የሱፐርቪዥን ሪፖርት ለምክር ቤቱ፣ ለኮሚሽኑና ለሚዲያ ተቋማት ኃላፊዎች ባቀረበበት ወቅት ነው።
መንግሥት የማያግባቡ ችግሮችን በመቅረፍና መልክ በማስያዝ የበለጸገች ሀገር ለመፍጠር ለህዝቡ የገባውን ቃል የመፈጸም ግዴታው መሆኑን አፈ ጉባዔው ገልፀዋል፡፡
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑን ስራዎች ህዝቡ እንዲገነዘብ በቂ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ስራ መሰራት እንዳለበትም አስገንዝበዋል።
ተሳታፊና ተባባሪ አካላትን መርጠው ባጠናቀቁ ክልሎች የአጀንዳ ልየታ ስራዎች ሊጀመሩ እንደሚገባም አፈ-ጉባዔው ማሳሰባቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል አቶ እጅጉ መልኬ ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በአራት ክልሎች የተሳታፊ እና የተባባሪ ልየታ ስራውን እንዳከናወነ አስረድተዋል።
በሱፐርቪዥን ስራው የተደራጀ የመረጃ አያያዝ መኖሩን፣ ለተመረጡ ተሳታፊና ተባባሪ አካላት ስልጠና መሰጠቱንና የኮሚሽኑ ስራ የተሳለጠ እንዲሆን መንግስት ያደረገውን ድጋፍ ቋሚ ኮሚቴው በጥንካሬ የተመለከታቸው ጉዳዮች መሆናቸውን አብራርተዋል።
በሌላ በኩል ስለ ኮሚሽኑ ተግባርና ኃላፊነት ለማህበረሰቡ በቂ ግንዛቤ አለመፈጠሩን፣ በክልል ተባባሪ አካላት የሴቶች ተሳትፎ አናሳ እንደሆነ እና በተሳታፊ ልየታ የተወሰኑ ቀበሌዎች አለመካተት በክፍተት የታዩ አበይት ጉዳዮች መሆናቸውን ቋሚ ኮሚቴው ማረጋገጡን አስገንዝበዋል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!