Fana: At a Speed of Life!

መከላከያ ሚኒስቴር በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 42 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር በዋግኸምራ ዞን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች በ42 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር 5 ሺህ ኩንታል የስንዴ ዱቄትበመግዛት ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉን ያስረከቡት የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ÷የተደረገው ድጋፍ ከመከላከያ ሠራዊት አባላት የተሰበሰበ መሆኑን ተናግረዋል።
ሠራዊቱ የሕይወት እና የአካል መስዋዕትነት ከመክፈሉ በተጨማሪ ሕዝብ ሲጎዳ እና ማንኛውንም የድጋፍ ጥያቄ ሲያቀርብ ፈጥኖ የሚደርስ ሕዝባዊ ወገንተኝነቱን በተግባር የሚያሳይ ነው ብለዋል።
በሁሉም አካባቢዎች እንደ ሀገር ከተባበርን፣ ከተስማማን እና መደማመጥ ከቻልን የሚደርስብንን ማንኛውንም ችግርና ፈተና እናልፈዋለን ሲሉም ገልፀዋል።
ዜጎች በሀገሪቱ እየተፈጠሩ ያሉ የተለያዩ ችግሮችን ለመቀልበስ ጠንክረው በጋራ እንዲሰሩ ጥሪ ማቅረባቸውንም የመከላከያ ሠራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ ያመላክታል።
በዋግኸምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በሳሃላ ሙሉ ወረዳ ዝቋላ በ7 ቀበሌዎች፣ በአበርገሌ 10 ቀበሌዎች እና በሌሎች አካባቢዎች ከ285 ሺህ በላይ ዜጎች በድርቅ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተጠቁሟል፡፡
መከላከያ ሠራዊት ችግር ውስጥ ለሚገኘው ሕዝብ ላሳየው አጋርነትም የዞኑ አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.