አቶ ደመቀ በሱዳን አሁናዊ ፈተና ኢትዮጵያ ከሱዳን ሕዝብ ጎን እንደምትቆም ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሁናዊው የሱዳን ፈተና ኢትዮጵያ ከሱዳን ሕዝብ ጎን እንደምትቆም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡
አቶ ደመቀ መኮንን የሥራ ዘመናቸውን ያጠናቀቁትን የሱዳን ሪፐብሊክ አምባሳደር ጀማል አል ሼይክን አሰናብተዋል፡፡
አቶ ደመቀ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷የኢትዮጵያና ሱዳን ግንኙነት በሕዝብ ለሕዝብ ትስስር የዳበረና የወንድማማቾች መሆኑን አውስተዋል፡፡
አምባሳደር ጀማል ይህ ግንኙነት ይበልጥ እንዲጠናከር ላደረጉት ከፍ ያለ ጥረት እና አስተዋጽኦም ምስጋና አቀርበዋል፡፡
አቶ ደመቀ በአሁናዊው የሱዳን ፈተና ኢትዮጵያ ከሱዳን ሕዝብ ጎን እንደምትቆም ማረጋገጣቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
የሱዳን አንድነት ተጠብቆ ሱዳናውያን በሚያምኑበትና በሚመሩት የሠላም ሒደት አስቸኳይ የተኩስ አቁም ስምምነት ማድረግ እና ዘላቂ ሠላም በሱዳን ማስፍን አስፈላጊ እንደሆነም አንስተዋል።
አምባሳደር ጀማል አል ሼይክ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ሀገራቸው እንደሆነች እና በሥራ ዘመናቸው ከተለያዩ ተቋማት ለተደረገላቸው ከፍ ያለ ድጋፍ አመስግነዋል።
ከሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘም ኢትዮጵያ የሱዳን አንድነት በተጠበቀ መልኩ ግጭት እንዲፈታ እና በጦርነቱ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ሱዳናውያን ለምታደርገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!