Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ከ32 ሺህ በላይ አባወራዎች እየተደገፉ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ምክንያት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ከ32 ሺህ በላይ አባወራዎች ድጋፍ እየተደረገ ነው ሲል የክልሉ ቡሳ ጎኖፋ ገለጸ።

የክልሉ ቡሳ ጎኖፋ የሎጂስቲክ ምላሽና መልሶ ማቋቋም ዳይሬክተር አቶ ደበላ ኢታና በቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ በባሌና ምስራቅ ባሌ፣ እንዲሁም በምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች ከዚህ በፊት በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው አባወራዎች ምግብ ነክ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

ከ32 ሺህ በላይ አባወራዎች የምግብ ነክ ድጋፍ እየቀረበላቸው እንደሆነም ነው የተናገሩት።

በዚሀ ዓመት ብቻ ከ500 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የምግብ ነክ ድጋፎች መቅረባቸውን አቶ ደበላ ተናግረዋል፡፡

በታሪክ አዱኛ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.