በጋምቤላ ክልል የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የዓሣ ምርታማነትን እንዳሳደገ ተመላከተ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር በመጀመሩ የተፈጠረው ምቹ ሁኔታ የዓሣ ምርታማነትን ለማሳደግ አስተዋጽኦ ማበርከቱን የጋምቤላ ክልል ግብርና ቢሮ አመለከተ።
በክልሉ ያለውን የዓሣ ሀብት በአግባቡ ለማልማት እየተሠራ መሆኑንም ቢሮው ገልጿል።
በክልሉ ግብርና ቢሮ የእንሥሳት እርባታ እና መኖ ልማት ዳይሬክተር አቶ አንተነህ ተሥፋዬ እንዳስታወሱት፤ ባለፈው በጀት ዓመት በክልሉ ከ6 ሺህ ቶን በላይ ዓሣ ተመርቷል።
ክልሉ በዚህ ዓመትም ምርቱን ለማሣደግ አሥፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን እያሟላ እንደሚገኝ ጠቅሰው÷ የዓሣ ምርታማነት እያደገ መሆኑን ተናግረዋል።
በዋናነት የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የፈጠረው ምቹ ሁኔታ ምርቱ ከፍ እንዲል እያደረገ እንደሚገኝም ነው የጠቀሱት።
ክልሉ በዓመት ከ15 ሺህ እስከ 17 ሺህ ቶን ዓሣ የማምረት አቅም እዳለውም ተመላክቷል።
በሰሎሞን ይታየው
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!