ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን ሥምምነት መፈረሟ በዲፕሎማሲው ዘርፍ ያላትን የላቀ ተሳትፎ ያሳያል -አቶ እንዳሻው ጣሰው
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን የመግባቢያ ሥምምነት ሰነድ መፈረሟ በዲፕሎማሲው ዘርፍ ያላትን የላቀ ተሳትፎ ያሳያል ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ገለጹ፡፡
አቶ እንዳሻው÷ኢትዮጵያ ከሶማሌ ላንድ ጋር የባሕር በር የምታገኝበትን የመግባቢያ ሥምምነት ሰነድ በመፈረሟ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡
በመልዕክታቸውም÷ኢትዮጵያ በየጊዜው እየገጠሟት ያሉ ፈተናዎችን በጽናት እየተሻገረች ለሕዝቦች የላቀ ብልጽግና በትጋት እየሰራች ነው ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
የባሕር በር ስምምነቱ ኢትዮጵያ በወጪ እና በገቢ ንግድ ላይ እያካሔደች ላለው እንቅስቃሴ የኢኮኖሚ ዋልታ ከመሆኑም ባለፈ ለጀመረችው የእድገት ጉዞ ፈር ቀዳጅ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡