Fana: At a Speed of Life!

ነጋሽ ዋጌሾ  (ዶ/ር ኢ/ር) ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን ሥምምነት በመፈረሟ መደሰታቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ኢትዮጵያ የባህር በር የምታገኝበትን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ በመፈረሟ የተሰማቸው ደስታ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን የመግባቢያ ሥምምነት ሰነድ ከሶማሌ ላንድ ጋር በዛሬው ዕለት ተፈራርማለች።

ስምምነቱን ተከትሎም ነጋሽ ዋጌሾ  (ዶ/ር ኢ/ር) ለክልሉ ሕዝብ እና ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም÷ባለፉት ጊዜያት ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባሕር በር እንደሚያስፈልጋት ብርቱ ትግል ስታደርግ ቆይታለች ብለዋል።

የባሕር በር የማግኘት ስምምነት ሰነዱ ኢኮኖሚያዊ ፣ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን በአፍሪካ ቀንድ ለማጠናከር የሚያግዝ መሆኑንም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.