ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበት የመግባቢያ ሥምምነት በመፈረሙ ተቋማት የደስታ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን የመግባቢያ ሥምምነት ከሶማሊላንድ ጋር መፈራረሟ ተከትሎ የተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ተቋማት የደስታ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ታሪካዊ ነው የተባለውን የመግባቢያ ሠነድ በትናንትናው ዕለት በአዲስ አበባ መፈራረማቸው ይታወቃል፡፡
ይህን ተከትሎም የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ባስተላለፈው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት÷ የተገኘው የባሕር በር የኢትጵያን ስብራት የጠገነና የትውልድን የዘመን ቁጭት የመለሰ መሆኑን አስታውቋል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በበኩሉ÷ ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት ያደረገችው የትብብርና አጋርነት ስምምነት ሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገት ላይ የላቀ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ÷ የመግባቢያ ሠነዱ የኢትዮጵያ መንግሥት በሰጥቶ መቀበል መርሕ እና ለጋራ ጥቅም ከጎረቤቶች ጋር የመሥራት ፍላጎትና አቋምን መልሶ የሚያፀና ነው ብሏል።
እንዲሁም ኢትዮጵያ በቀጠናው ሰላም እና ደኅንነት የሚገባትን ሚና እንድትጫወት የተሻለ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን አመልክቷል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!