Fana: At a Speed of Life!

የሀገር አቀፍ ሕግ አውጪዎች የጋራ የምክክር መድረክ በሐረር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር አቀፍ ሕግ አውጪዎች የጋራ የምክክር መድረክ በሐረር ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምህረት፣ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ የፌዴራል፣ የክልል እና የሁለቱ ከተማ መስተዳድር ምክር ቤቶች አፈ-ጉባዔዎች ተገኝተዋል፡፡

በመድረኩም የሀገር አቀፍ የምክክር ኮሚሽን ስራ አፈፃፀም እና የሱፐርቪዥን፣ የፍርድ ቤቶችና የፍትህ ተቋማት ትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈፃፀምና የሱፐርቪዥን ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የቀጣይ አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.