Fana: At a Speed of Life!

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አዲስ አሰራር ወደ ስራ ማስገባቱን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለተገልጋዮች አዲስ አሰራርን ወደ ስራ ማስገባቱን አስታወቀ።
በበይነ መረብ አማካኝነት የትምህርት መረጃ ማጣራት፣ የትምህርት ማስረጃ ለሌላ ተቋማት መላክ ፣ ድጋሚ የትምህርት ማስረጃ መውሰድ፣ የትምህርት ማስረጃን ማረጋገጥ በምዝገባ ወቅት የሚያጋጥምን የስም ፊደላትን ጉድለት ማስተካከል እንደሚቻል ነው የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) የተናገሩት።
አገልግሎቱን ለማግኘት ተገልጋዮች በቴሌ ብር እና ንግድ ባንክ በኩል ክፍያ መፈፀም እንደሚኖርባቸው ተመላክቷል፡፡
ከዚህ በኋላ በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ቅርንጫፎች እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ180 ሀገራት፣ በአካል እንዲሁም በውክልና ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።
ይህ የበይነ መረብ አገልግሎት ተገልጋዮችን ከእንግልት ይጠብቃል ተብሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከቀጣይ ወር ጀምሮ ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ምዝገባ እንደሚጀመርም ነው የተመላከተው።
የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎትም የተሰጠውን ሀላፊነት ለመወጣት ዝግጅቶች ማድረጉን ስራ አስፈፃሚዋ ሀና አርአያስላሴ ተናግረዋል።
 
በፍቅርተ ከበደ
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.